nedir | Неотсортированное

Telegram-канал nedir - ዐውደ ጥበብ

4629

በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን ለ አስተያየት @lalaA60 @nunned

Подписаться на канал

ዐውደ ጥበብ

ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAEoOnK2wLQlq_TGQVA

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ጂጂሙ
የማስታወቂያ ስራ
ባነር እና እስቲከር ህትመት
በባነር
ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ
የተለያዪ ዝግጅቶን ያድምቁ
(ሠርግ፣ልደት ....ወዘተ)
በስቲከር
የቢሮና የሱቅ መስታወቶን
እንዲሁም መኪናዎን ያስውቡ
ለበለጠ መረጃ
@lalaA60 ን ይጠቀሙ ስልክ +251912122725
+251910596099
+251937921871

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

~ ራሴው ማበዴ ነው… …#4 ~
(ሜሪ ፈለቀ)
"ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?”
"ማለት? ስለምን?”
"እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ
ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣
የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።”
ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።
ራሴን አውቄ ሀላፊነትን መሸከም ከቻልኩበት ጊዜ ጀምሮ
ለሚያውቀኝ ሰው ወይም በምንም አጋጣሚ ቢሆን ድጋሚ ላገኘው
ለምችለው ሰው ስለራሴ ተናግሬ አላውቅም። ነገር ውስጤ
ተቆልሎ የሆነ ዓይነት እምቅ ሀይል ሆኖ እንደ ኒውክለር ሊፈነዳ
የመሰለኝ ወቅት ላይ አንድ ሶስቴ ከዛን ቀን በኋላ ፊታቸውን
አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች የተሰማኝን ዝርግፍግፍፍፍ
አድርጌ ከመፈንዳት ተርፊያለሁ። አንዷ ‘ነገ አረብ ሀገር ልሄድ
ነው።’ ያለችኝ ፀጉር ቤት ያገኘኋት ሴት ናት። ፀጉራችንን ተስርተን
ስንወጣ ለማኪያቶ ካፌ ተቀምጠን ያወራኋት። ሁለተኛው ናዝሬት
ለስራ ሄጄ ያረፍኩበት ሆቴል ብቻዬን ራት ስበላ አይቶኝ ‘እንብላ’
ባለኝ ሰበብ ያወቅኩት ጎልማሳ ነው። (ሊበላኝ(ሊያባላኝ) ባሰበ
ምሽቱን የተበላው።) ሶስተኛው ከቂሊንጦ ስመለስ ሊፍት የሰጠኝ
ሽማግሌ ነው። አንዳቸውንም ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ
አይቻቸው አላውቅም። ስሜን አያውቁም ፣ ማን መሆኔን ፣ የት
መሆኔን አያውቁም……… ሳወራላቸው ነገ ሲያዩኝ ምን
ይሰማቸዋል? አልልም…… ሳለቅስ ወይ ስዝረከረክ ይዳኙኛል
አያሰጋኝም…… በነሱ ፊት መሸነፌ ወይ ተስፋ መቁረጤ ድክመቴ
አይሆንም። …… ለምንም ግድ የለኝም። ልግባቸው
ላደናግራቸውም ጉዳዬ አይደለም። የተሰማኝን በሙሉ ዘርግፌ
ተንፍሻለሁ።
ለሚያውቀኝ ሰው እንደዛ አላደርግም። ለሚያውቁኝ ሁሉ
(ከቤተሰቦቼ ውጪ) ያቺ አልቅሳ የማታውቀው ፣ብርቱዋ ፣ ደካማ
ጎኗን ማንም የማያውቅባት፣ መጠቃቷን ማንም የማያውቅላት… …
የጉብዝና ምሳሌ የሆነችዋን ራሔል ነኝ።
"ፍትህ አንተ ደግሞ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስራህን እርግፍ
አድርገህ ትተህ እኔን ስራ አድርገኸኛል። am fine!! በቀን አስሬ
ቢሮዬን የምትከፍተውን ነገር አቁም። please?” አልኩት። ብዙ
ቀን ብዬዋለሁ ሰበብ እየፈለገ በጥያቄ ይወጥረኛል እንጂ።
"እሺ። ከፈለግሽኝ ግን አለሁ።” ብሎኝ ቆይቷል። ከቢሮዬ ግን
አልወጣም። ከወንበሩም አልተንቀሳቀሰም። ሁሌም የማስበው
የኖህ ታሪክ ትዝ አለኝ። ከውሃ ጥፋቱ በኋላ ኖህም ገበሬ ሆነ።
ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ። …… በድንኳንም
ውስጥ ራቁቱን ሆነ ታናሹ ልጁ ካምም የአባቱን እርቃን ባየ ጊዜ
ተሳለቀ። በአባቱ ገመና ሙድ ያዘ። ሁለቱ ልጆቹ ያፌትና ሴም ግን
እርቃኑን እንኳን እንዳያዩበት አክብረውት ፎጣ በትከሻቸው
አድርገው የኋሊት እየተራመዱ የአባታቸውን እርቃን ሸፈኑ… ……
ኖህም ካምን ረገመው… ………… ይመስለኛል። ሲመስለኝ
ሲመስለኝ……… የካም ነገድ የአክሱምን ልጅ ወለደ……
የአክሱምም ልጅ ልጆች በወንድምና ወዳጃቸው ገመናና ድክመት
ሲደነቋቆሉ… … ሲሸረዳደዱ…… አንዱ የአንዱን ድክመት ሲጋለቡ
ኖረው ኖረው። የእንጀራ እናቴ አባት ላይ ደረሱ። እሳቸውም ቀንደኛ
ሸርዳጅ የሆነች ትውልድ አፈሩ……… ምናምን ምናምን………
የኖርኩት ዘመን የተረዳሁት አብዛኛው ሰው ከትልቁ ስኬትህ
ውስጥ እንኳን ምናምኒት የምታክል ውድቀትህን ወይ እንከንህን
ይፈልጋል። ካገኘብህ አለቀልህ። ሰማይ ያከለ ስኬትህን የጎመንዘር
በምታክል እንከንህ ያጣፋልሃል።
"ፍትህ?”
"አቤት ቦስ?”
"ነገ ሰርጉን ትሄዳለህ እንዴ?”
"አወና!! እንዴ ቆይ ቆይ…… ትሄዳለህ ነው ትመጣለህ? ያ ማለት
የእህትሽ ሰርግ ላይ አንቺ አትኖሪም ማለት ነው? ኦ……ኬ …… I
think ይሄ ኬዝ ካሰብኩት በላይ ሊመስጠኝ ነው። ምንድነው
እሱ?”
"ምንም big deal አይደለም። መሄድ አለመሄድህን ለማወቅ
ነው። አበቃ!! የሆነ ታላቅ ግኝት ያገኘህ አታስመስለው።”
"እሄዳለሁ።” ብሎኝ ዓይኖቹን ዓይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ ስሜቴን
ሊጨምቅ ይታገላል።
"መልካም።” አልኩት ድምፄ ከስሜቴ ጋር አብሮ ሲወርድ
እየታወቀኝ።
"በቃ?” ብሎ አፈጠጠብኝ ከተቀመጠበት መንጭቆ እየተነሳ።
"በቃ ሌላ የምትዪኝ ነገር የለም?”
"እንዴ? ምን እንድልህ ነው የምትፈልገው?”
"አላውቅም!! ብቻ ከቤተሰብሽ ጋር በተያያዘ አንድ እንዳላውቅ
የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስለኛል። አላውቅም!! ንገሪኝ ማወቅ
ያለብኝ ነገር ካለ ከሌላ ሰው ከምሰማው በፊት ንገሪኝ!”
"Excuse me? ከሌላ ሰው ከመስማትህ በፊት?ራስህን ምን ቦታ
ላይ ነው የሰቀልከው ባክህ?” ሆኖ እንደማያውቀው እየጯጯህን
ነው።
"Sorry boss! ራስን መስቀል አይደለም። እንደጓደኛ……”
"እኔና አንተ ጓደኛሞች አይደለንም! ደግሞ ቦስ አትበለኝ። አለቃህ
አይደለሁም። ስም አለኝ። እኔና አንተ የስራ ባልደረቦች ብቻ ነን።
የሚያገናኘንም ስራ ብቻ ነው።” ንግግራችን የማያስፈልገውን
ያህል ቁጣ እየተቆጣሁ እንዳለሁ ራሴን ስሰማው አውቃለሁ። ግን
ቁጣዬ ምክንያቱ ፍትህ ብቻ አልነበረምና መመጠን አልችልም።
"እሺ ጓደኛሽ አድርጊኝ? I mean not just for sayin… … real
ጓደኛሽ ልሁን?።” አለኝ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ እና ከኔ
በተቃረነ እርጋታ። ሁኔታዬ ራሴኑ አሳፈረኝ። እሱ ላይ የምጮህበት
ምንም ምክንያት የለኝም። ፀጥ አልኩ። ጠረጴዛዬ ላይ በአንድ
መቀመጨው እየተቀመጠ
" I know አንቺ በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ። ያ ማለት ግን ሰው
አያስፈልግሽም ማለት አይደለም። ያንቺን ጭንቀት ማወቄ ላንቺ
ያለኝን ቦታ አይቀንሰውም። በምታልፊበት ነገር ሁሉ ውስጥ አልፈሽ
እዚህ መገኘትሽ ምን ያህል ጠንካራ ሴት መሆንሽን ያገዝፍብኛል
እንጂ።” አለኝ የፍትህ በማይመስል እርጋታና ብስለት።
"ለምን ብለህ ምክንያቱን አትጠይቀኝ። እባክህ ሰርጉን አትሂድ?”
ማለት ብቻ ነበር የመጣልኝ ሀሳብ
"እሺ።” አለ እንደዘበት። ከዛም ያልሰጠሁትን እጄን ፈልቅቆ
እየማለ “ ይኸው !ቦስ ይቅርታ ራሔል ሙች! አልሄድም።
ከፈለግሽ በቤተሰብሽ ኬዝም አልገባም። ያ የሚያስደስትሽ ከሆነ
ምክንያትሽንም ማወቅ አልፈልግም። ራስሽ ፈልገሽ እስካልነገርሽኝ
ድጋሚ አልጠይቅሽም። ግን አንድ እንድታደርጊልኝ የምፈልገው
ነገር አለ!” እያለኝ ስልኬ ጠራ። ከቤት ነው። አንስቼው ስለእማዬ
በሰማሁት ነገር እግሮቼ ዛሉብኝ። የብርትኳን ቢላዋ አንስታ ታፋዋ
ላይ ሰክታለች። ሰራተኛዋ እየተርበተበተች ነው የነገረችኝ።
ስለእማዬ በሰማሁ ቅፅበት ፍትህን ረስቼዋለሁ።
"ምንድነው እሱ? ምንድነው? እናትሽ ምን ሆነው ነው?” አፌ
ቃላት መትፋት አቃተው። ምንም አላስፈቀደኝምም።
አልጠየቀኝምም። ስልኬን አንስቶ መልሶ ደወለ። ልሄድ ቆሚያለሁ።
ግን መንቀሳቀስ ከበደኝ። ከሰራተኛዋ ጋር እያወራ እንደሆነ
አውቃለሁ። ግን አልሰማውም። ኮቴንና ቦርሳዬን ሰብስቦ እጄን
መንጭቆ ይዞኝ ሲወጣ እግሬን ለመራመድ ማዘዜን ባላውቅም
ተከትዬው መኪናው ጋር ደርሻለሁ። በሩን ከፍቶ መኪናው ውስጥ
ሲያስገባኝ፣ ስንሄድ፣ ከሰራተኛዋ ጋር ሲደዋወል፣ እቤት ይዞኝ
ሲገባ… …… ጆሮዬ ጭውውውውው ይልብኛል። ጭንቅላቴ የሆነ
ከባድ ነገር እንደተጫነብኝ ለአንገቴ ከብዶታል። …………
★ ★ ★ አሁንም በድግምጋሚ አልጨረስንም ★ ★ ★

https://t.me/joinchat/AAAAAE9OUq05Q82nGhE9qw

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ለምርቃት ለሠርግ ለልደት ስጦታ ይፈልጋሉን

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

#ሌላኛው_አለም
ክፍል 2
ህይወት ከሜላት ጋር በአዲስ መልክ ካስተዋወቀች በኋላ ዛሬ የመጀመሪያዬን ቀን ልጀምር ነው የማይገፋ የሚመስለው ለሊት ተገፎ ሰማይ በብርሃን እንደተሞላች የወፎቹ ዝማሬ ቢያበስረኝም አይኔን ግን መግለፅ ፈርቻለው ምክንያቱም አይኔን ብገልፅ የአዲስ ቀን ጅማሮዬን ተከትሎ ብዙ የማጣቸው ነገሮች እንዳሉ አወቃለው ለምሳሌ አስከ አሁን ሜላት ወደ ክፍሌ አልመጣች ይህ ማለት ዘወትር እንደ ጠዋት ፀሀይ ያለ ስስት ትሰጠኝ የነበረውን የእህትነት ፍቅሯን እያጣሁት ነው ወይም አጥቼዋለው ማለት ነው እኔ ደሞ እንደሱ አንዲሆን አልፈልግም ስለሆነም አሷ ጉንጬን ሳትስመኝ ሄዳለች ብዬ ከማስብ አይኔን ሳልገልጥ ሰዓቱ ገና አንደሆነ ባስብ ይቀለኛል እያደረኩት ያለሁትም ይሄን ነው ሜላት መቼም ቢሆን ጉንጬን ሳትስመኝ ቀኗን አትጀምርም ስለማቃት ነው
.
.
.
አላልኳችሁም በር ተንኳኳ ሜላት ናት አሁን አንዴ ደግማ ታንኳኳና አዱሻ ብላ ትገባለች
.
.
.
ዛሬ ምን ሆናለች እቺ ልጅ መቼም በኔ መቀለድ አይሰለቻትም ዛሬ ደሞ ምን አይነት ጨዋታ ጀመረች ዝም ብላ አትገባም እኔን ለማስለፋት ነው እንጂ.
.
.
.
"እትይ እንዳሉህ ምነው ያለ ወትሮህ አስጠበከን በሰላም ነው ወይ " ሰራተኛችን ነበረች ኤጭ ምን አይነት ድምፅ ነው ያወጣችው የሜላትን ድምፅ ጠብቄ ስለከፈትኩ ነው መሰለኝ ድምፇ ኮሰኮሰኝ
"መጣው ስራ ይዤ ነው" በያቸው ብዬ ከሸኘኋት በኋላ በጀርባዬ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ አሁን ህይወቴ በልጅነቴ ከማቀው 1 ተረት ጋር ተመሳስሎብኛል
በድሮ ጊዜ አንድ በጣም ስግብግብና ቋጣሪ ሰውዬ ነበር እናም ይህ ሰውዬ አንድ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ነበረችው እናም ሰውዬው የወርቅ እንቁላል በመጣሏ ቢደሰትም በቀን አንድ መጣሏ ምንም አላረካውም ነበር በዚህም የተነሳ በቀን እየቆጠበች የምትሰጠኝን የወርቅ እንቁላል እንደ ጡረተኛ ቁጭ ብዬ ከምጠብቅ ለምን አሷን ገደዬ ሙሉውን አልወስድም ብሎ አሰበ አስቦም አልቀረም ዶሮዋን አረዳት ግን ምን ዋጋ አለው በቀን አንድ የወርቅ እንቁላል የምትሰጠው ዶሮ የአንድ ቀን ምሳ ብቻ ሆና አረፈችው የዕድሜ ልክ ወርቁን አጣ
ሜላትም ለኔ እንደዛ ናት የወርቅ እንቁላል የምትሰጠኝ ዶሮ ዶሮዬን ነው ያረድኳት ምንም እንኳን ቢላውን እሷ ብትሰጠኝም እኔ እንቁላሉ ብቻ ይበቃኛል ማለት ነበረብኝ ግን ምን ዋጋ አለው ስጋ(ግብረ) ሆነና ከእንቁላል በለጠብኝ
.
.

"አንተ ልጅ ዛሬ ምን ሆነሃል አትመጣም እንዴ አባትህ እየጠበቀህ ነው እህትህም ያለወትሮዋ አንተን ስትጠብቅህ ከትምህርት መቅረቷ ነው በል ቶሎ ና "የሚል የእናቴ ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ ሜላት አስከ አሁን አለሄደችም? ሜላት አስከ አሁን አለመሄዷ ደስ ቢያሰኘኝም አህትህ የምትለው ቃል ግን አዕምሮዬ ውስጥ ገብታ እረፍት ነሳችኝ ነገር ግን መቆየቷ ያመጣልኝን ደስታ እንዲያደፈርስብኝ ስላልፈለኩ ልብሴን እንደነገሩ ከለበስኩ በኋላ ፊቴን በፍጥነት ተጣጥቤ በውጥረት ወደ ተሞላው ማዕድ ሄድኩ ከዚህ በፊት ሜላት እስከዚህ ሰዓት ቆይታ አታውቅም ዛሬ ግን ቆየች ለኔ ብላ ነው የቆየችው የሰራነው ነገር መኝታ ክፍሌ እንዳትመጣ አድርጎ ድፍረት ቢያሳጣትም ከዘገየውበት ማዕድ ላይ ግን ተቀምጣ እየጠበቀችኝ ነው የዛሬው ቁርስ በተላያዩ ትንግርቶች የተሞሉ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም ገና ከመምጣቴ አባቴ "ምን ሆነህ ነው ልጅ ተስፋዬ አበበ እንደዚህ ይደረጋል " አለኝ አባቴ ሁሌም ልጅ ተስፋዬ አበበ ነው የሚለኝ አንድም ቀን አዱሽ ብሎ ጠርቶኝ አያውቅም ሁሉም ነገር ትርጉም ሲኖረው ነው ጥሩ ይላል
"ምን የዛሬ ልጅ ስልክ ላይ ተጥዶ እያመሸ በየት በኩል ንቁ ይሁን ብለህ ነው" አለች እናቴ እንደመሳቅ እያለች
"ቢሆንም ከዚህ በፊት የሌለበትን እንቅልፋምነት ላዛውም በኔ ቤት " አለ አባቴ እውነቱን ከበፊትም ጀምሮ በጠዋት እንድንነሳ ይፈለግ ነበር የራሳቹ ቤት ስትገቡ እንደራሳቹ በኔ ቤት ግን እንደኔ እንድትሆኑ እፈልጋለው አንድ ቀን ትክክል እንደሆንኩና ምን አይነት ውለታ እንደዋልኩላቹ ይገባችዋል ይለን ነበር ትላንትም ከሜላት ጋር በስሜት ማዕበል ስንዋኝ ቀስቃሽ ያጣነው እሁድ በመሆኑ ነበር ወትሮንም ቢሆን በሰንበት የተሰራ ስራ በረከት የለውም ትል ነበር አማዬ ለዚህም ነው የዘላለም በረከቴን ያጣሁት እሁድ እሁድ ምንም ቢፈጠር እረፍታችን እንደተከበረ ነው በፈለግንበት ሰዓት መነሳት እንችላለን ሌላ ቀን ግን የማይታሰብ ነው
ወንበሩን ስቤ ከተቀመጥኩ በኋላ በመተፋፈር በመፈራራትና በመደባበቅ በታጀበው ቁርስ ላይ ለ5 ደቂቃ ያህል በዝምታ ከበላን በኋላ "ምንድነው ዛሬ ያላወኩት ጉድ ... የተፈጠረነ ነገር አለ እንዴ " ሲል አባቴ ዝምታውን ሰበረው
ምን እንደሚል ያልገባት እናቴ "ምን ተፈጠረ ነው የምትለው ስትል" ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት "አሁን የማየው ነዋ ምን ሆነው ነው የሚተፋፈሩት እስከ አሁን አይን ለአይን አልተያዩም እኮ ጉድ እኮ ነው ምን መሆናቹ ነው የተፈጠረ ነገር አለ አንዴ ብሎ ወደ ሜላት ዞረ ሜላትም "እረ የለም ማለቴ አለ አይ ትንሽ አናዶኝ አኩርፎኝ ማለቴ አኩርፌው ነው አንጂ ሌላ ምንም የለም"ብላ እየተርበተች መለሰች
"ልፋ ብሎህ ነው እንጂ ሁለቱ እንደሆኑ በትንሽ በትልቁ መኮራረፍና መጣላት ልማዳቸው ነው ደሞ በመሀላቸው ሰው አስገብተው አያቁም እራሳቸው ይፈቱታል" አለች
"አንደዛ ከሆነ ጥሩ " ብሎ ባይዋጥለት መብላቱን ቀጠለ እኔም ሜላትን ቀስ ብዬ አየት አደረኳትና መብላቴን ቀጠልኩ
*****ይቀጥላል***************
https://t.me/joinchat/AAAAAEGznayjbWng0o2h7Q

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ትላንት ውሾቹ ደስታችን ላይ ጥላሸት ባይጥሉ ኖሮ...
ይሄኔ...
መሪያችን በአለባበሱ ስላስተላለፈው መልዕክት፣
ስለ ንግግሩ ይዘት፣
ስለህዝቡ ህብር፣
'ተቃቀፉ' ብሎ ስንተቃቀፍ ስለገነፈለው ዕንባችን፣
ስለተያዙ መፈክሮችና ሰንደቅዓላማዎች፣
ስለፖሊሶቻችን አገልጋይነት፣ (አወይ የጊዜ መለወጥ!!! የኛ
እንደሆኑና የነሱ እንደሆንን በዐይን ስንግባባ)
.
በጋሽ ጥላሁን 'እናት ሃገር ኢትዮጵያ'
በአብረሃም ገ/መድህን 'ሃንቀውታ'
በነዋይ ደበበ 'ሃገሬን አልረሳም'
በሃጫሉ 'ማሳን ገማ'
እና በብዙ በቡዙ ሃገርኛ ሙዚቃዎች በደስታ ያዜምነውን፣.
.
ከኋላችን ቆሞ ደቀቅ ባለ ሰውነት፣ ኮሰስ ባለ ድምጽ
<Down with black racism apartheid!' የሚለው
አሳዛኝ ሰውዬ (የድሮ መምህር የመሠለ )
ከፊትለፊታችን ቆመው.. ዶክተር አቢይ ተናገሮ
እስኪጨርስ፣ ከኃይማኖት አባት ቃለምህዳን እንደሚቀበል
ምእመን.. ሁለት እጃቸውን ከትከሻቸው በላይ ከፍ አርገው
ስለተከታተሉት አባት፣
ብቻ ስለብዙ ብዙ ውብ ትዕይንቶች እናወራ ነበር።
.
እሱ በንግግሩ ስላስገባን ቃል። በስራችሁ በትምህርታችሁ
በይቅር ባይነታች ከጎኔ ስትቆሙ ነው አመሠገናችሁኝ
የምለው ብሎ ስላስጨበጠን አደራ... ስለቀጣይ የለውጥ
ጉዟችን ነበር ስናወራ የምንውለው። ስናወራ
የምንከርመው።
.
የኔ ጠቅላይ ምኒስትር... የህዝብ አባት!!
እንደ ሌቦችና እንደ ሆዳም ዘረኞች ምኞት ሳይሆን እንደ
አንድነት ወዳዱ፣ እንደ ፍትህና ፍቅር ፈላጊው አብዛኛው
ኢትዮጵያዊ፣
ለዘመናት በሃገሩ ሃገር እንደሌለው ሲሰማው ለኖረ
ባይተዋር ህዝብ...
ለዘመናት ስትግጡት ኖራችሁ በትዕግስቱ ዝም ስላላችሁ
ስለዚህ ህዝብ ሲል... ከሞት ተርፎልናል።
.
የኛ መሞትና መቁሰል እንኳን ተራ ነገር ሆኖ ለምደነዋል።
ያሰባችሁት ዕልቂት አልሆነም አልተሳካም፣ ህዝብም
ከህዝብ አይባላም።
እውነት ታሸንፋለች።
ስለዚህች የክፋት ጥንስሳችሁ ትከፍላላችሁ!
Join us @nedir

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

የፀጥታ ሀይሉ 2 ወንዶች እና 1 ሴት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሉዋል
For more update news
Join us @nedir

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ጠሚ ዶ/ር አብይ መስቀል አደባባይ ተገኝተዋል

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

የዛሬ አስገራሚ ፎቶዎች ካሉዋቹ በ @nunned ላይ ላኩዋቸው ለአሸነፉ ተወዳዳሪዎች የመፀሀፍ እና የተለያዩ ሽልማቶች አዘጋጅተናል

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

Live from gonder to support pm dr abiy ahmed ali

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ጣጥር ስድስት ዓመታት ያልፉ ነበር። እንደዛሬው ደስታህንም
ፍሬህንም አታይም ነበር። " አለችኝ የሆስፒታሉ አልጋ ላይ
በአፍንጫዋ ነጭ ቱቦ ገብቶ፣ በፕላስቲክ ያለ ደም ከአናቷ
ተንጠልጥሎ እንደተጋደመች።…… በአይኖቿ ጠርዞች እንባዋ
በቀጭኑ እየወረደ………
ኤልሲ ልታገባ አልነበረም……………
ኤልሲ አላገባችም……………
ኤልሲ እኔን ማፍቀሯን አቁማ አታውቅም…………
ፀፀትን አከናነበችኝ።
★★★ጨርሰናል★★★

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

★★★ ሞቴን ቀማኝ………#3★★★
(ሜሪ ፈለቀ)
በህይወቴ የሚመጡ ሰወች ሁሉ ኮከቦች ሊሆኑ አይችሉም።
ወይ የማያደምቁ ወይ የማይሞቁ ሰወች በምን ስሌት ኮከቦቼ
ይሆናሉ? ብዬ ማሰብ ጀመርኩ።
ያሬድ እንደዚያ አይነት ሰው ነው። ምን ያህል እንደሆነ
የማላውቀውን የአባቱን ንብረት ስለተካፈልኩት እምብርቴ ላይ
ቆሟል። …… አየኸኝን ላስታምመው የተስማማሁት ንብረቱን
ከልጁ ጋር እኩል እንደሚያካፍለኝ ከማወቄ እጅግ አስቀድሞ
ነው። …… ቀድሞ ነገር ንብረት ይኑረው አይኑረውም አላውቅም።
…… ለጥቆ ነገር ከንብረቱ በላይ የመኖር ተስፋዬን ያለመለመ
ሰው ነው። …… ሰልሶ ነገር ንብረት ምኔም ያልሆነ ሴት ነኝ።
……
አየኸኝ አዲሳባ መጥቶ ብዙም ሳይቆይ ሆስቲታል ገባ……
የከተማው ድንግርግር፣ ለማየው ነገር ሁሉ እንግዳ መሆኔ……
ሳይለቀኝ የህይወቴ ፈርጥ ኮከብ የህይወት ክሩ ጫፍ ላይ
መሆኑን አወቅኩ። …… ህይወት ተለዋጭ ብትሆን የምለውጠው
ሁሉ ይመስለኛል። …… አዲስአበባ እንደደረስን ያለውን ንብረት
በሙሉ ከልጁ ጋር እንዳካፈለን ነገረን። …… ከዚያች ዓረፍተ
ነገር በኋላ ያሬድ ቃል አልተነፈሰም። …… ሆስፒታል በቀን አንዴ
ብቅ እያለ አባቱን ያየዋል። …… አያናግረውም። ……
"ከአባቴጋ ያላችሁ ግንኙነት ምንድነው?" አለኝ የሆነ ቀን
"ልጄ ሲለኝ አልሰማህም? ልጁ ነኛ!" መለስኩለት
"እንቦቃቅላ ጨቅላ አደረግሽኝ እንዴ አንቺው? ተሱ
እንዳልተወለድሽ አውቃለሁ! ምን ሲሆን አየሽው በይ? እንደየት
እንደየት ብለሽ አጠመድሽው? ንብረቱን ብለሽ እንጂ
መቼም……" …… የገጠር አነጋገር ለዛው ያዝ እያደረገው ……
አልጨረሰውም
"በናትህ ተወኝ! ከፈለግክ ሁሉንም ንብረት ውሰደው!! አንተ
አባትህ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ የሚያስጨንቅህ ንብረት ነው?"
አልኩት አልመለሰልኝም።
"እንኳን እኛ የወረስነው የለፋበትም አልኖረበት!" ቀጠልኩ
"ምንድነው የምዘላብጂው?" ብሎ ትቶኝ ሄደ።
አየኸኝ አፉ ሲያዝ ብዙም አልቆየም። ሀኪሞቹ ሆስፒታል
መቆየቱ ምንም ጥቅም ስለሌለው ወደ ቤት እንዲሄድ ነገሩት።
…… ቁጭ ብሎ ሞትን መጠበቅ እንዴት ያማል? ለኔ ስቃይ
ሆነብኝ። አየኸኝ ግን በስቃይ ውስጥ ሆኖ እንኳን ፈገግታው
አልከሰመም።……
"ካልተሻለው ለምን ወደ ቤት አመጣሽው?" አለኝ ያሬድ በሆነው
ቀን
"የሚሰጡት ህክምና ስለሌለ እዛ መተኛቱ ምንም ጥቅም
የለውም።" መለስኩት
"ታዲያ የተሻለ ሀኪም ቤት ይሂዳ?"
"ቀልድ ነው የያዝከው? ምን ያለኸው ክፉ ነህ? ሲሆን ባለቀች
እድሜው በፍቅር ልትሸኘው ሲገባህ……" ብዬ መጨረስ አቃተኝ።
ከእንባዬ ግብ ግብ መግጠም አልፈለግኩም። ተሸነፍኩ።
አነባሁ።
"ይታከም ማለት ክፋት ነው?" አለ ለዘብ ብሎ
ይሄኔ ግራ ተጋባሁ። አንድ ያልገባኝ ነገር መኖሩ ተገለጠልኝ።
……
"ለመሆኑ በሽታው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?" አልኩት።
በጭንቅላቱ ውዝወዛ አለማወቁን ነገረኝ። ይሄኔ ሁሉም ግልፅ
አለልኝ። አባቱ እንደሚሞት አያውቅም።
"አባትህ ሀብቱን የተናዘዘው ለምን መሰለህ ታዲያ?" አልኩት
"ሲሻለው ገዳም እንደሚገባ ነው የነገረኝ።"
ግራ ተጋባሁ። ለምን ደበቀው? አየኸኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን
ምን ያሬድ ማወቅ እንዳለበት አሰብኩ። …… ከአባቱጋ እንዴት
እንደተዋወቅን ስነግረው… …
"አንድ ቀን ካያት ሴት እኩል ንብረቱን ያካፍለኛል?" ሲል ውስጤ
ሲረግብ ተሰምቶኛል።
"በማየት ከሆነ እኮ እንደውም ካንተ ቀድሞ ነው ያየኝ።
እውቂያችን ብዙም አይራራቅም።" አልኩት ብስጭት ብዬ
"ልጁ ነኝ‘ኮ" አለኝ ጥርሱን ነክሶ……
"አባትህ ከሳምንት ያለፈ እድሜ የለውም። ይሞታል። ……
የጭንቅላት እጢ ነው ያሉት በሽታውን……" ስላበሳጨኝ ሌላ ቦታ
እያየሁ ነው ያወራሁት። እስከምን እንደሰማኝም አላውቅም።
ከአጠገቤ ተነስቶ ወደአባቱ ክፍል ሮጠ። …… ተከተልኩት። ……
"ለምንድን ያልነገርከኝ?" እያለ በሩን በርግዶ ገባ። አየኸኝ
እስከዛሬ ያላየሁት መመሳቀል ፊቱ ላይ ታየኝ። …… አፍን ሊከፍት
ታገለ… ቃላቶቹ እዛው ከንፈሩ ላይ ድምፅ ሳይሆኑ ይዋጣሉ።
እጁን ሊያነሳ ሞከረ…… ጣቱን ከማንቀጥቀጥ ያለፈ ማድረግ
አልቻለም። ……
"25 ዓመት እስኪሆነኝ ሳትፈልገኝ… … ልትሞት ስትል ለምን
ፈለግከኝ? ሀዘን ልታሸክመኝ? ለምንስ እውነቱን አልነገርከኝም?
በፀፀት ልትፈጀኝ?"
እውነቱን ለማውራት አነጋገሩ ያሳዝናል። ደረቱን እየደቃ ጮክ
ብሎ ነው የሚያወራው። …… እየሰማሁት እያለቀስኩ መሆኔ
የገባኝ እንባዬ የአገጬ ደርዝጋ ሲደርስ ነው።
"ለምን አገኘኸኝ? አባት እንደሌለኝ አምኜ እየኖርኩ ነበር። ለምን
መጣህብኝ? ለምን እንደተውከኝ አልቀረህም? ለምን
አገኘኸኝ?" እያለቀሰ መሆኑን ሳይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ
ግራ ተጋባሁ። የአየኸኝ ስቃይ አሰቃየኝ። እንባዬን ጠርጌ ያሬድ
አጠገብ ደረስኩ። እጁን ያዝኩት። መነጨቀኝ። አጥብቄ ድጋሚ
ያዝኩት።
"ምን?" አለኝ እያፈጠጠ
"ያሬድ መናገር አይችልም እኮ እያስጨነቅከው ነው።" አልኩት…
… አልሰማኝም መንጭቆኝ ሄዶ አባቱ አልጋ አጠገብ በጉልበቱ
ተነጠፈ።
"ታውቃለህ? ትልቅ እስክሆን የሆነ ቀን አባቴ ሊፈልገኝ ይመጣ
ይሆናል ብዬ እጠብቅህ እንደነበር? አታውቅም! ታውቃለህ እናቴ
ብዙ ሆና እንዳሳደገችኝ? አታውቅም! ታውቃለህ አባቴን ብዬ
ባስጨነቅኳት ቁጥር እንደምትንሰቀሰቅ? አታውቅም!! ምንም
አታውቅም!! በዛ ሁሉ የናፍቆት ጥበቃዬ ዝር አላልክም። ልትሞት
ስትል ግን አገኘኸኝ። ለምን? ምን አደረግኩህ? ለምን ሌላ
ናፍቆት ትደርብብኛለህ? ምናለ ክፋትህን እንዳመንኩ ብኖር?"
…… ስርቅታው አላናግር አለው። ……
"ወየው…… ወየው…… ወየው ፈጣሪዬ ምን በደልኩህ?" ብሎ
ሲጮህ እሪ ብዬ አብሬው መጮህ አምሮኝ ነበር። ……
ጭንቅላቱን ይዞ እሪታውን አስነካው። አየኸኝ የአንድ አይኑ
እንባው ወደጆሮው ሲሄድ አየሁት። …… ያደረግኩትን ያወቅኩት
ካደረግኩት በኋላ ነው። …… እሱ እንዳደረገው መሬቱ ላይ
በጉልበቴ ተንበረከኩ። …… አጥብቄ አቀፍኩት። ……
አልታገለኝም። ድምፁን አውጥቶ ተንሰቀሰቀ። ……
……
………
አሁንም አልጨረስንም……

https://t.me/joinchat/AAAAAE9OUq05Q82nGhE9qw

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

" ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ
ነው "
© በዕውቀቱ ስዩም
....... አሜሪካ ውስጥ በአብርሃም ሊንከን ዘመን የነበረ
ሆስፒታል ዛሬም አለ።
.
እንግሊዝ ሀገር በሄድኩ ጊዜ የዛሬ ስንት እና ስንት መቶ አመት
አካባቢ ሼክስፒር በጠጣበት ቡና ቤት ጠጥቼ ሼክስፒር
በሸናበት ታዛ ስር ሸንቼ ወደ ሀገሬ የመመለስ ዕድል ገጥሞኛል።
.
ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ዕድል ማግኘት አይታሰብም።
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ቦታ የምታገኘው መንግስትን ብቻ
ነው።
.
ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከሳምንት በፊት ጤና ጣቢያ የነበረው
ከሳምንት በኋላ ፖሊስ ጣቢያ ሆኖ ታገኘዋለህ እናም በሽተኛ
ለመጠየቅ ያመጣኸውን ፍራፍሬ እስረኛ ጠይቀህበት
ትመለሳለህ።
በዚህ አይነት:-
ከሳምንት በፊት ሙዚየም ከሳምንት በኋላ ጅምናዚየም።
.
ከሳምንት በፊት ላይብረሪ ከሳምንት በኋላ እኔ ነኝ ያለ ግሮሰሪ።
.
የሰውም ለውጥ ፍጥነት እንዲሁ ነው:-
ከወር በፊት ተላላኪ ከወር በኋላ አስመጭና ላኪ።
.
ከአመት በፊት የከባድ መኪና አሽከርካሪ ከአመት በኋላ
የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ።
ከአመት በፊት አድማ በታኝ ከአመት በኋላ የኳስ ተንታኝ ሆኖ
ታገኘዋለህ።
.
በነገራችን ላይ የኳስ ነገር ሲባል አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ከሶስት
ወራት በፊት መሰለኝ በአትሌቶችና በባለስልጣናት መካከል
በአዲስ አበባ ስታዲየም የኳስ ግጥሚያ ተደርጎ ነበር። እና
ኮመንታተሩ አትሌቶች ኳስ ሲይዙ
'ኦ ••••• ቀነኒሳ ኳስ በእጁ ነክቷል አደገኛ ስህተት ' እያለ ትችት
ሲያዘንብባቸው ይቆይና ባለስልጣኖች ኳስ ሲይዙ ይቅለሰለሳል።
.
.
'አሁን ጀነራል ኳስ ይዘዋል ' ። ጀነራል አታለው አለፋ ለማለት
ፈለገና አታለው የሚለው ቃል ክብር የሚነካ ስለመሰለው ጀነራል
መስዋዕትነት ከፍለው አለፉ

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

⇨ለልብ እርካታን የሚለግሱ ምክሮችን
- ምርጥ ምርጥ ገለፃዎችን
- ማራኪ እና ድንቅ ንግግሮችን
-ብትናንሽ ቃላቶች ትላልቅ ምክሮችን
-አዝናኝ ቪዲዮዎች እና ፒክቸሮችን
የሚያገኙበት ማራኪ አርኪ ተወዳጅ ቻናል
👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEsELwTdAsxelyWlBw
❄️❄️❄️❄️❄️

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

እናንተ ተደዋወሉ፡፡ እኔ ደብዳቤ ፅፌያለው፡፡ መልሷን
በናፍቆት እጠብቃለው፡፡
.
ይድረስ ካብ ፍቕረይ ረዊና
.
ለክለተ ባዶ አመታት ጠፊኡ ዝነበርሽ ጊዜታት ሁሉ ለአሃደ
ጊዜ ካብ አይምሮዬ ጓዳ አልጠፊኡም፡፡
.
ናይ 1990 ኣመተ ምህረት ጀሚሩ ንለያየን ንመንግስት
ግጭት ናይ ዘንድሮ አመት ተፈትኡ፡፡ ልአብይ አህመድ
ያቐንለይ! በፃእም ደስ ኢብል ነገር እዬ፡፡
.
መአረይ
.
አብዚ ኢትዮጵያ ብዙ ነገርታት ተፈጢሩ ለአለፈ ክለተ ባዶ
አመታት እኮ፡፡ ናይ አባይ ፀሃዬ ለስኳር ፋብሪካ ቀሪጥፎ
በሊኡ፡፡ ናይ አቦይ ስብሃት አርጂቶም ስኳር በሽተኛ ሆይኖ፡፡
ናይ መለስ ዜናዊ ሞይተ፡፡ ሁሉ ጠንካራ ዝነበረ ህወሓት
ሰብ ተደምሲሱ፡፡ ግናስ ዳንኤል ብርሃነ፣ አብርሃ ደስታ
ገለመሌ ዝብሃል ሰብ መፂኡ ኒረስ ለነሱ ድማ ለክለተ ጊዜ
ተደምሲሱ፡፡ አሁን ስጋት ዝብሃል ነገር የለን፡፡
.
ሀዲሽ ዘመን ተበሲሩም፡፡ ናይ ከረን እመፂእየ አለሁ፡፡ ድማ
አብረን ኮይነን እንኸድ አይለን ለቀይ ባህሪ ዳር ዳርታት ካብ
አሸዋ እንጫወት አለና፡፡ ንፍቕ ኢልካ እኮዬ፡፡ ፍቕረይ!

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ስልኮት ውስጥ 3 ብር አሎት? እንግዲያውስ ከታች ያለውን ቁጥር ፅፈው ይደውሉ ይደውሉ 100 mb free internet packege ያገኛሉ ይሞክሩት
እርግጠኛ ነኝ ይደሰታሉ መልካም ውሎሎሎሎሎ
.
.
.
👍👍👍*999*1*2*2*1*1*0937921871*1#👍👍👍

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

አድራሻ ቦሌ መድሀኒያለም ሞርኒንግ ስታር አንደኛ ፎቅ ⌚️💍👓👑

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

#ሌላኛው_አለም
ክፍል 3
1 2 3 እያለ ከሜሊ ጋር እንደ ድሮው መሆን ካቃተን 7 ቀናት ተቆጠሩ። ልክ የዛሬ ሳምንት በዚህ ሰዓት ነበር ከሜሊ ጋር የህይወታችንን ከባዱን ስህተት የሰራነው ...ከዛን ቀን ጀምሮ አስከ ትላንትናዋ ዕለት ድረስ ሜሊን ላናግራት ብሞክርም ዛሬ አሞኛል፣በጣም ስለደከመኝ ዛሬን ልተኛ፣ዛሬ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም እና መሰል ምክንያቶችን እየሰጠች ትሸሸኝ ጀመር
እኔም ላስጨንቃት ስላልፈለኩ ሁሉንም ምክንያቷን አክብሬ ዛሬ ላይ ደርሻለው። ዛሬ ግን የመጣው ቢመጣ ሳላናግራት አላድርም ምክንያቱም ሜሊ ዛሬ ቀኑን ሙሉ ቤት ነው የምታሳልፈው። የዛሬን አያድርገውና እኔና ሜላት እሁዳችንን በሚያምርና ደስ በሚል ሁኔታ ነበር የምናሳልፈው እሁድን ሳስብ ሜሊን አለማሰብ ይከብደኛል የብቻዬ እሁድ የለኝም። ሜሊ የሌለችበትን እሁድ የሚገልፅልኝ የኢንግሊዘኛው ትንታኔ ነው «sun day»ሜሊ የሌለችበት እሁድ day ብቻ ነው የሆነ የማላቀውና ተራ ቀን «sun» እነዲኖረው የምታደርገው ሜሊ ነች የህይወቴ ፀሀይ! እርግጥ ነው በአንድ ሁለት አጋጣሚዎች እሁድን ያለሜሊ አሳልፌ አውቃለው እናም እነዛ እሁዶች ከሰኞም የባሱ አስቀያሚና ከባድ ነበሩ ስለዚህ አሁን በኔና በሜሊ መካከል የተፈጠሩትን መሰናክሎች ቶሎ አስወግጄ ፍቅራችንን ወደ በፊት ክብሩ መመለስ አለብኝ ያለበለዚያ ግን..... ይቅርታ .....በአሁን ሰዓት ያለበለዚያ ብዬ ማሰብ አልፈልግም።
*********************
ሜሊን ላናግራት ወደ ክፍሏ ስሄድ ለባብሳ ልትወጣ ስትል ደረስኩ
"ሚሊ አንዴ ላናግርሽ?" አልኳት ገና ክፍሏ ከመግባቴ ሰላምታም በቅጡ ሳልሰጣት አሷም ነገሩ ስለገባት "አሁን አልችልም ሰላም ጋር ልሄድ ነው" አለች .....(ሰላም ማለት የሜሊ ብቸኛ ጓደኛና የእኔ ደሞ የአንድ ሰሞን ፍቅረኛ ነበረች ... ሰላምን ያወኳት በሜሊ ሲሆን እንዴት እንደተዋወኳትና በምን ምክንያት አንደተለያየን ሌላ ጊዜ እነግራቹኋለው )
"እሺ በቃ ስትመጪ እናወራለን ክፍሌ ሆኜ እጠብቅሻለው " አልኳት "አሺ ካልደከመኝ አመጣለው" አለች እየተቅለሰለሰች
"ሜሊ ሙች አትምጪና ትጣይኛለች በአንቺ ደግሞ ምዬ እንደማልዋሽ ታውቂያለሽ"አልኩ ከልቤ ብስጭት ብዬ "ኧረ አዱሻ አትበሳጭ ከፈለክ አሁንም ቢሆን አናግረኝ ሰላምን በኋላ አገኛታለው"አለች በሁኔታዬ ተደናግጣ "አይ ችግር የለውም አሁን አሷን አግኛት .... እሷን አግኝተሻት ስትመጪ እናወራለን" ብዬ ከክፍሏ ወጣው።
****************
ነገሩ እኔ አንዳሰብኩት ቀላል አይደለም ሜሊ ካሰብኩት በላይ ርቃ ተጉዛለች ..... ስለ ሴቶች ብዙ አውቃለው ብዬ ባልኩራራም ስለ
ሜሊ ግን የማላውቀው ነገር ይኖራል
ብዬ አስቤም አላውቅም ነበር ....ግን ምን ዋጋ አለው እኔ የማቀው እሷ እንዳውቀው የፈቀደችልኝን አንጂ ማወቅ ያለብኝን አይደለም:: አንዳውቀው የፈቀደችልኝ ነገር ደሞ ካላወኩት ነገር ጋር ሲነፃፀር የሰማይ ና የምድር ያህል ልዩነት አለው። ...
ትላንት ሜሊ የነገረችኝ ነገር ምንም ከአዕምሮዬ ሊጠፋ አልቻለም ነገሩ ሁሉ ባላሰብኩት መንገድ እየተወሳሰበ ከአቅሜ በላይ ሆኗል። .... አሁን በዚህ ታሪክ ውስጥ ያለነው ተጎጂዎች 3 ሆነናል ...እኔ ....ሜሊና .......ሰላም
እንዴት?
****ይቀጥላል ***
https://t.me/joinchat/AAAAAEGznayjbWng0o2h7Q

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

#መደመር_ቅኔ_ነዉ !! ((1)) "
-
( ምንተስኖት ዋቆ)
-
ይነጋል ታያለሽ ፣
ብዬ የገጠምኩልሽ ፣
የሶስት ሺ አመት : ታላቋ ወይዘሮ ፣
ብርሀን ወጣልሽ : ፅልመት ተዘርሮ ።
ዛሬ ላይ ቢነጋም : ከመቼዉም ማልዶ ፣
#ለማ አንድነትሽ : #አብይሽን ወልዶ ።
-
-
( #2010_ዴቻ )

ETHIOPIAN

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ፍንዳታው ይህን ይመስላል

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

#ሌላኛው_አለም
ክፍል 1
ከውስጥ የለበሰችውን ፓንትና ጡት ማስያዥያ የሚያሳይ ስስ ቢጃማ ላይ ጋውን ጣል አድርጋ "አዱሻ አልተነሳህም እንዴ" እያለች ወደ ክፍሌ መጣች እኔም ከእንቅልፌ እንደመንቃት እያልኩ " አቤት ሜሊ አረ ተነስቻለው መቼም ጉንጬን ሳትስሚኝ ቀንሽን መጀመር እንደምትፈሪ እያወኩ እንዴት እተኛለው "
ብዬ ፈገግ ስል
"ኧረ ባክህ ሞዛዛ ጉረኛ ማን ያንተን ጉንጭ ይፈልጋል ብላ ከንፈሬን በስሱ ሳመችው" አላመንኩም
"ምነው ደነገጥክ ችግር አለው" አለችኝ
"ኧረ የለውም ከዚ በፊት ስመሽኝ ስለማታውቂ ገርሞኝ ነው"
"ሃሃሃ ነው እንዴ እንደዛ ከሆነማ በደንብ ይግረምህ" ብላ ከንፈሬን ደግማ ሳመችኝና ከላይ የለበሰችውን ጋውን አወለቀችው እኔም ግራ በተጋባ ድምፅ ሜ ... ላ ት ስል
"ዝም በል " ብላ በሩን ዘጋችና ቢጃማዋን በዝግታ አወለቃ በፓንትና በጡት ማስያዣ ብቻ ቀረች
" ምን አያደረግሽ ነው" አልኩ አሁንም ግራ እንደተጋባው "ምንም አንተን እያስገረምኩህ ነው ይሄንንስ አንተ ታወልቀዋለህ ወይስ እኔ ላውልቀው" አለች ስሜት በተቀላቀለበት ድምፅ እኔ የምለው አጥቼ ዝም አልኩ
"እሺ ዝምታም መልስ ነው ይላል አባዬ"
ብላ ጡት ማስያዣዋን ልብ በሚሰቅል ሁኔታ ቀስ ብላ ፈታችው እኔ የማየው ነገር ሁሉ ህልም ሆኖብኛል በመቀጠል ቀስ ብላ ፓንቷን በዝግታ አወለቀችውና
"አሁን ደሞ ያንተ ተራ ነው"
ብላ ወደኔ መታ ከአልጋዬ ላይ አስነሳችኝ አኔም የማረገው ጠፍቶኝ ዝም ብዬ ተነሳው
"ምነው ተርበተበትክ የመጀመሪያህ ነው አንዴ"
ብላ ከንፈሬን ሰማ ከላይ የለበስኩትን ልብስ አወለቀችው በመቀጠል ቁምጣዬን አውልቃ ወደ አልጋው ገፈተረችኝና እላዬ ላይ ወጥታ ትስመኝ ጀመር እኔም ግራ መጋባቱን ትቼ የቀረበልኝን ሲሳይ አጣጥመው ጀመር ትንፋሿ በጣም ይጋረፋል አቅሌን ልስት ምንም አልቀረኝም ሜላትን አስከዛሬ እንደማላቃት ገባኝ ለካ እንደዚህ የምትጣፍጥ ማር ነች ለትንሽ ግዜ ከተሳሳምን በኋላ "እንደዚህ ብቻ ነው የምናደርገው" ስትል ጠየቀችኝ
እኔም ምን ለማለት እንደፈለገች ስለገበኝ ወገቧን ይዤ ገለበጥኳትና ከንፈራን ስሜ ሜላትን በአዲስ ማንነትና በአዲስ ተግባር ከአዲስ ተዋወኳት እስከዚች ቅፅበት ድረስ ግን ሜላትን እንደ እህቴ ነበር የማያት የዛሬ 15 ዓመት የ7 ዓመት ልጅ እያለው ነው አባቴ የባለ ውለታዬ ልጅ ናት ብሎ ቤት ያመጣት ያኔ ሜላት ስትመጣ የ5 ዓመት ልጅ ነበረች ከዛን ቀን ጀምሮ እስከዚች ደቂቃ ድረስ መወለድ ቋንቋ ነው ብለን እንደ እህትና ወንድም እየተያየን አደግን ግን ምን ዋጋለው ማደጋችን ያመጣው ተራ ዕውቀት እህቴን አሳጣኝ ለዚህ ነው ማወቅን የምፈራው ከሷ ጋር የማደርገው ወሲብ በጊዜው ቢያስደስተኝም ከዛን በኋላ እየተሰማኝ ያለው ፀፀት ከአዕምሮዬ በላይ ነው ምክንያቱም
ሜላት እህቴ ስትሆን ነው የሚያምርባት፣ሜላት እህቴ ስትሆን ነው ችግሬን የማካፍላት፣ሜላት እህቴ ስትሆን ነው ከአባቴ ጋር ስጣላ ከለላ የምትሆነኝ፣ሜላት እህቴ ስትሆን ነው እኔ ሙሉ ሰው የምሆነው ይህንን ሁሉ ነገር ነው በአንድ ቅፅበትያጣሁት ከዚ በኋላ ሜላት እህቴ መሆን አትችልም ግንኙነታችን ወደ ሌላ አለም አምርቷል .....
*ይቀጥላል******

https://t.me/joinchat/AAAAAEGznayjbWng0o2h7Q

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ከጠሚ ዶ/ር አብይ ንግግር ቡሀላ የእጅ ቦንብ ፈንድቱዋል እስካሁን ባለን መረጃ የ3 ሰው ህይወት አልፉዋል 😭😭😭

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

Live from desi

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

Live from addis ababa

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

★★ ሞቴን ቀማኝ…… #4★★
(የመጨረሻ ክፍል)
"እታባ ‘አባትህ ጥሩ ሰው ነው። አንዳች እክል ካልገጠመው
በቀር እንዲህ አይጨክንብንም።‘ ትለኝ ነበር "
ያሬድ ለአየኸኝ እየነገረው ነው። ……የማንጎ ጭማቂ በማንኪያ
ሊያጠጣው እየሞከረ…… ማብቂያ የሌለው ከሚመስል የሰዓታት
ዝምታና ብቸኝነት በኋላ ከአባቱ አጠገብ ተቀምጦ ስለ እናቱና
ስለራሱ ማውራት ሆኗል ልምዱ…… አየኸኝ ባይመልስለትም
ልጁ አጠገቡ ተቀምጦ እየደባበሰ ያለማቋረጥ ሲያወራው ፊቱ
ይፈግጋል። ………
"…… እኩያዬ እኮ ነው። …… ስላሸነፍኩት አባቱ ተደርቦ ገፈተረኝ
እና እግሬ ወለም አለኝ።…… ከዛ አባቴን ካልወለድሽ ብዬ እህል
አልቀምስም አልኳት።……" በትውስታው ፈገግ ብሎ ቀጠለ "……
አለቀሰች። ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ በአንተ ስትመረር
የሰማሁት ያኔ ነው። …… አሳዘነችኝ። ……"
በሩ ላይ ቆሜ እሰማዋለሁ። ……
"በቃ እረፍ ትንሽ…… በወሬ አደከምሁህ" ብሎ ሊነሳ ሲል
አየኸኝ ፊቱ ተከፋ……
"ትንሽዬ ተኛና ደግሞ አጫውትሃለሁ።" ብሎ የአባቱን እጅ
ሳመው……
የተቀሩት ቀናት እንደዚህ አለፉ። ……
"ወንድሞች እንደነበሩህ ነግሮህ ነበር?" አልኩት የሆነ ቀን
"ምንም አልነገረኝም። ምንም አልጠየቅኩትም ነበር።" መለሰልኝ
በጉጉት ። ያጫወተኝን በሙሉ ነገርኩት። ቃል ሳይተነፍስ ሰማኝ።
"ምስኪን አባቴን!" አለ ተነስቶ ወደ አባቱ ክፍል እየሄደ። ……
"የሰው ልጅ ተፈጥሮ ፈጣሪውን ነው የሚመስል፣ መልካም ነው።
በህይወቱ በሚያልፋ ክፉና መልካም ተጎዳኝ ክስተቶች ክፉ
ይሆናል እንጂ በተፈጥሮ የከፋ ሰው የለም።" ይለኝ ነበር አባዬ
ያሬድን አስቤ የገባኝ ይሄ ነው።በህይወቱ ያለፉ መከራዎች ሁሉ
መንስኤ የአባቱ እናቱን ማስረገዝ እንደሆነ ነው የሚያምነው።
…… ላለመማሩ እና የገጠር ወጣት ሆኖ ለመቅረቱ መንስኤ
አባቱ እሱን አለመፈለጉ እንደሆነ… …… እሱ አቅሙ ደርሶ አርሶ
መዝራት እስኪችል ከእናቱ ጋር በጥልቅ ድህነት ዘመናቸውን
ገፍተዋል። …… ለሁሉም ምክንያት የሚያደርገው አባቱን ነው።
……
አባቱ ሊሞት መሆኑን ሲሰማ ምሬቱን ረሳው፣ ያለፈ መከራውን
ተወው…… መከፋቱን ዘንግቶ ለአባቱ አለቀሰለት።……
ድምፁን የሰማሁ ስለመሰለኝ ተነስቼ ወደ አየኸኝ ክፍል ገባሁ።
ያሬድ መሬቱ ላይ ተንበርክኮ ድምፅ አልባ ለቅሶ ሲያለቅስ
ደረስኩ። …… ያንን ሞቴን የቀማኝን የአየኸኝ ለቅሶ የመሰለ
መንሰቅሰቅ…… ያን እንባ የሚቀማ ለቅሶ የመሰለ ፍቅፍቅታ… …
እራሱን አባቱን ይመስላል። …… አንጀት የሚያላውስ አይነት… …
የተፈጠረው ገባኝ። …… እሪ አልኩ። …… ድንኳን ተቀምጦ
የቅርብ ወዳጁ እያለቀሰ እንደደረሰው ለቀስተኛ የኔን እሪታ
ሲሰማ የሚይዘው አሳጣው። …… ኡኡ ብሎ አለቀሰ። ……
በለቅሶና በእንባ ብዛት የራስን ሀዘን ያራግፉታል እንጂ ለአየኸኝ
የነፍስ ስንቅ አይሆን ነገር ተላቀስነው……
ይህ የአየኸኝ ህይወት ፍፃሜ ነበር። የእኔ ህይወት ጅማሬ……
የያሬድም ሌላ የህይወት ምዕራፍ ጅማሬ…… ወዳጅ ነኝ ያለ
በተሰበሰበበት ተቀበረ። ……
………
………
……
አየኸኝ ከሞተ ወዲያ አዲሳባ መቀመጡ ምንም ስላልተመቸኝ
ወደ ቀዬዬ ከተመለስኩ ሰነባበትኩ። ያሬድም ጠበቃው የንብረት
ክፍፍሉን ጉዳይ ፈር እስኪያሲዝ እናቱን ይዞ ሊመለስ ወደ
ቀዬው ወረደ። ጠበቃው እንደነገሩኝ ከሆነ እውነት የማይመስል
ንብረት ባለቤት ሆኛለሁ። በእርግጥ ምንም ላልነበራት ሴት ይሄ
ሁሉ ምኗ ይሆናል? ……
አዲስ ህይወት እጀምራለሁ? አዲስ አበባ እገባለሁ?
የምጀምረው ህይወት ደስተኛ ያደርገኛል? አዲስ የኑሮ ልምድን
ካልተለማመድኩ ይሄ ሁሉ ንብረት በዛች በእርምጃ በምትለካ
ቀዬዬ ምን አደርግበታለሁ? …… የቱንም አውቆ መወሰን አቃተኝ
እና ማሰቡንም ተውኩት።……
……
……
ጠበቃው ያዘመመች ጎጆዬ ድረስ ሲመጣ ወራት መንጎዳቸው
ገባኝ። …… የነገረኝን የገንዘቤን መጠን የኔታ አላስቆጠሩኝም።
… እንኳን ልሾፍረው አዲስ አበባ ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ
የተሳፈርኩበትን መኪና… … የመኪና ባለቤት መሆኔን ነገረኝ።
……
…… የአየኸኝ ኑዛዜ ያለውን ንብረት በሙሉ እኩል ካካፈለ በኋላ
ቤቱንም እንድንካፈል ያዛል። ……
"ያሬድ ሊያማክርሽ ይፈልጋል ወደ አዲስ አበባ መሄድ አለብን!"
አለኝ ጠበቃው…
እዚህም ብቀመጥ የምፈትለው ጉዳይ ስላልነበረኝ ተስማማሁ።
……
……
……
………
ያሬድን ሳገኘው እንደ አብሮ አደግ ወዳጅ ተሰማኝ። በሰፊ እጆቹ
አጀብ ደረቱ ላይ ቆየሁ። …… የምን እንደሆነ ያለየሁት ለቅሶ
አለቀስኩ። አባበለኝ። …… እናቱ ተቆጥተው ለቅሶዬን
አስቆሙኝ… …
"ምን አሰብሽ?" አለኝ በሁለተኛው ቀን ሲመሻሽ ገደማ
"ምን ላስብ?"
"የሌላው ንብረት በግልፅ ስለተካፈለ አስቸጋሪ አይደለም። ቤቱን
እንዴት እናድርገው?" አለኝ
"ኸረ ሌላው ገንዘብ ይበቃኛል። ቤቱን ከእናትህ ጋር ኑሩበት።
አይሸጥም።" መለስኩለት
"እንዲህ እንድትዪኝ አይደለም።" አለኝ ቅር እየተሰኘ
"ያለው መፍትሄ ምንድነው? ሸጦ መካፈል አይደል? ወይም
አንዳችን የአንዳችንን ድርሻ ከፍሎ ቤቱን መጠቅለል? እኔ ካንተ
ገንዘብ ተቀብዬ ቤቱን አልሸጥልህም። ተቃራኒውንም
አላደርግም። ……"
"ሌላ መላ አይኖርም?" አሉ እናትየው የያሬድን አይን አይኖች
እያዩ… … አስቀድመው የፈተሉት ወግ እንዳለ ያስታውቅባቸዋል።
"ምን አስባችሁ ነው?" አልኳቸው ተራ በተራ እያየኋቸው።
"ለምን አብረሽኝ አትኖሪም?" ሲል አይኖቹ አላዩኝም። ድምፁ
ውስጥ ጥያቄ አይደለም ያለው… … ልመና ነበር። …… አብሮ
መኖር…… አብሮ ከያሬድ ጋር መኖር……
"ባክሽ አትመለሽ?" አለ ቀጠለና… …
"በኔ ይሁንብሽ ልጄ… … ሞክረሽ ካልሆነ የፈለግሽው ይሆናል።"
አሉኝ እናትየው
"እሺ!!" አልኩኝ በደመነፍስ ወዲያው ‘ምኑን?‘ ብባል መልሱን
የማውቀው አይመስለኝም።
ያሬድ ከተቀመጠበት ተነስቶ እጆቼን እያገላበጠ ሳመኝ።
እናትየው በእልልታ ቤቱን አቀወሱት። ይሄኔ እዚህ ቤት አብሮ
ከመኖር ያለፈ የተጨዋወቱት ፈትል እንዳለ ገባኝ። ……
……
………
አሁን ጨርሰናል።

https://t.me/joinchat/AAAAAE9OUq05Q82nGhE9qw

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

★★★ የማይጠራ ድፍርስ ★★★
(ሜሪ ፈለቀ)
"ለምን ዋሸሽኝ?" አልኳት በሆነው ሁሉ ግራ እንደተጋባሁ።
የቆዳዋ መገርጣት፣ የሰውነቷ ክሳት ከድሜዋ ሀያ ዓመታት
አስረጅቷታል። ከድምፅዋ ውጪ ምኗም የኔን ውቧን ኤልሳን
አትመስልም።
"አሳመምሺኝ ኤልሲ… …… ትተሽኝ ከሄድሽበት ጊዜ ይልቅ አሁን
ጎዳሽኝ።"
ያልኩትን ሰምታኛለች። እንዳልሰማ ችላ ብላ
"ልጅህ ነው? ቆንጆ ልጅ ወልደሃል!!" አለችኝ
በሩን ተደግፎ ሲያዳምጠን የቆየውን ዘሩባቤልን እያየች።
"አዎ ትንሹ ልጄ ነው። " አልኳት የማስበው እየተመሳቀለብኝ።
ዛሬ የባለቤቴ እህት ታማ እሷን ለማየት ነበር ከባለቤቴ ጋር ወደ
ሆስፒታሉ የመጣነው። ዘሩባቤል ከበሽተኛዋ ክፍል ወጥቶ
ሲመለስ ክፍሉ ጠፍቶት ሲደናበር ነው የኤልሲ ክፍል የገባው……
ልፈልገው ስወጣ አንደኛዋ ነርስ ጠቆመችኝና ስገባ አይኔ ያየውን
ማመን አቃተው……… የኔዋ ኤልሲ አልጋው ላይ ተጋድማለች።
ከስድስት አመታት በፊት እየሳሳሁላት ነው ትታኝ የሄደችው
ትታኝ የሄደች ዕለት:—
ስልኳንም ቤቷንም ለሁለት ሳምንታት ዘግታ በጭንቅ ካንገላታችኝ
በኋላ ጠዋት ደውላ ቀጠረችኝ። ኤልሲን እወዳታለሁ።……
የመውደድ ልኬት ሚዛኑ እስኪያንስብኝ እወዳታለሁ።…… ድምፅዋን
ስሰማ ከየትኛውም ሀሳቤ ወጣለሁ፣ ስትነካኝ የሲኦል አፋፍ ላይ
ቆሜ እንኳን ቢሆን እስቃለሁ፣ ስትስመኝ እንኳን ያለሁበት ሁኔታና
ቦታ ስሜም ይጠፋኛል።…… ስትስቅ ‘እናትህ ሞታለች‘ እያለችኝ
እንኳን ቢሆን እገለፍጣለሁ።…… ስታለቅስ ‘የሞተው አባቴ ከሞት
መነሳቱን‘ እየነገረችኝ ቢሆን እንኳን አለቅሳለሁ። ………
……… ከኤልሲ ውጪ ያሉ ክስተቶች የሚወሰኑብኝ ለእርሷ
በሚፈጥሩት ስሜት ነው። ……
የልቤ ንግስት ፀሃይን የሚያስንቅ የፊቷ ፀዳል ከስሟል።
እንዳቀረቀረች
"ላገባ ነው!" አለችኝ። አሳቀኝ። ቀልድ እንደተነገረው ሰው ሳቅኩኝ
"መቼ ነው የምታገቢኝ?" አልኳት አገጯን በጣቴ ቀና አድርጌ
አይኖቿን እየፈለግኩ
"እየቀለድኩ አይደለም። ዳዊትን ላገባው ነው። ከዚህ በተሻለ
ከሀገር ውጪ የተሻለ ህክምና የማግኘት እድል አለኝ። ይዞኝ
ሊሄድ፣ ሙሉ የህክምናውን ወጪ ሊሸፍንልኝ ቃል ገብቶልኛል።"
የቃሏ ምሬት የእውነቷን እንደሆነ ያስታውቃል።…… ህልምም
መሰለኝ።
"ዳዊት ማነው? እንዴት? እኔስ? ቆይ ለምን? ……… "
ዳዊት:—
የዳዊት ማንነት ጠፍቶኝ አልነበረም። ዳዊትን ልታገባው መወሰኗን
እስከነገረችኝ ሰዓት ድረስ ዳዊት ማለት ለኔ ከሀገር ከመውጣቱ
በፊት ይከታተላት የነበረ ዶክተር ነበር። ልታገባው መሆኑን ካወቅኩ
በኋላ አምርሬ የምጠላው ሰው ሆነ። ኤልሲን አጥቼ ለኖርኳቸው
ህይወት አልባ ቀናት እሷን መውቀስ አይሆንልኝም እሱን
እንጂ…………
ህይወት አልባ ቀናት:—
አይኖቼን አላየቻቸውም።
"ተወኝ! ልታገኘኝ አትሞክር። አትረብሸኝ።" ብላኝ በተቀመጥኩበት
ጥላኝ ሄደች። ብቻዬን ሳይሆን አለምም አብራኝ የደነዘዘች፣
የፈዘዘች፣ የደነገጠች……… መሰለኝ። …… ኤልሲ የኔ ብቻ ሳይሆን
የአለም ፍቅረኛ የሆነች ይመስል…… አለም ሁሉ አብሮኝ የወረደ
መሰለኝ። …… ሁሉም ነገር ህይወት አልባ ሆነብኝ። ኤልሲን ላገኛት
በሞከርኩ ቁጥር ትርቀኝ እና እሷን የማገኝበትን መንገድ መዝጋት
ጀመረች።
"እርሳኝ!" ትለኛለች።
ወድጄ ነው እንዴ ጥላኝ የሄደችን ልጅ የማስባት?
አብራኝ ከእናቴ ማህፀን የወጣች ይመስል ብቻዬን ራሴን ማሰብ
አቃተኝ። ኤልሲ ያልነበረችበትን የዘመኔን ቀናት ላስታውስ
ተቅበዘበዝኩ።
መች ነበር የማውቃት:—
ራሴን ሳውቅ ኤልሲንም አውቃታለሁ። ሰፋፊ ክፍተት ያለውን የኛንና
የእነሱን ቤት በሚለየው የእንጨት አጥር መሀል ወደኛ ጊቢ
ስትሾልክ………… እናቴ ለሁለታችንም የሚበላ ሰጥታን
ስንጣላ………አባቷ እኔን ከፊት እሷን ከኋላ በሞተር ሳይክላቸው
ጭነውን ሲነዱ……… ኤልሲን ሁሌም ነው የማውቃት።
ምን ቀን ነው የወደድኳት?:—
አብረን ትምህርት ቤት ስንሄድ? ወንድ የፃፈላትን ደብዳቤ
አስነብባኝ ስቀና? ልብስ ሊገዛላት አብረን ሄደን ስትለካ በልብስ
ከልያት ቆሜ ልብሷን ስታወልቅ ሰርቄ ገላዋን ያየሁት ቀን?
ለክረምት ክፍለሃገር ሄዳ በናፍቆት የነደድኩኝ ወቅት?
‘ወድሻለሁ!‘ ስላት ፍንክንክ ብላ እየሳቀች ‘ምን አድርጌህ
ትጠላኛለህ? ‘ ብላ ያበሸቀችኝ እለት? የማትሪክ ውጤት
አምጥተን በደስታ አመኻኝታ ከንፈሬን የሳመችኝ እለት? አንድ
ዩንቨርስቲ ደርሶን በጉዞ አመኻኝተን አንድ ክፍል ስናድር ሰውነታችን
የተጋባ እለት?
በአንዱ ቀን ይሆናል የወደድኳት ወይም በሁሉም ቀናት ነበር
እወዳት የነበረው።
እሷ ያልነበረችበት የህይወት ዘመን የለኝም። ስትስቅ
ገልፍጫለሁ፣ ስታዝን አልቅሻለሁ……… ስትታመም አጣጥሪያለሁ።
ስትታመም:—
ተመርቀን ወደቤታችን የተመለስን ሰሞን ኤልሲ ድንገት ታመመች።
ከልቧ ወደሰውነቷ ደም የሚረጨው የደም አዘዋዋሪ ቱቦ ተዘግቷል
ተባለች። እጅግ በፈጠነ ቅፅበት ብዙ ለውጦች ተከወኑ።
የአካሏ ለውጥ:—
ተበላሸ የተባለው የደም ቱቦ በባእድ ነገር ተቀየረ። ይሄን ተከትሎ
ኤልሲ ብዙ ነገር ማድረግ እንደማትችል ተነገራት። ሙቀት
የበዛበት አካባቢ መቆየት ፣ የበዛ መደሰት፣ የበዛ ሀዘን፣ ወሲብ
ማድረግ፣ ማርገዝ ወይም መውለድ……… እንደማትችል አወቀች።
እነዚህ ነገሮች ራስን ከመሳት እስከ ሞት የሚያደርሷት ክስተቶች
ነበሩ።
የኤልሲ ለውጥ:—
ማታ ከስራ ወጥቼ ይዣት ወጣሁ። የናፈቀኝ ከንፈሯን ሳምኩት፣
መለሰችልኝ፣ ስትስመኝ ምንም አላስታውስ አይደል? ተንገብግቤ
ጎረስኳት………… ተመሳሳዩን አደረገች። ……… ከዛ በኋላ
የተፈጠረውን አላስታውስም። እጄ ላይ ራሷን ስታ መውደቋን
አየሁ። …………
………
………
ከቤተሰቦቿ ቤት ወጥታ ቤት ተከራየች። እቤቷ አልጋዋ ላይ ቁጭ
ብዬ መፅሀፍ አነብላታለሁ። ክንዴን ተንተርሳ እያዳመጠችኝ እጆቿን
ልብሴን ከላዬ እንዲገፉላት ላከቻቸው። ……… እጇን በቀስታ
ከልክዬ አገላብጬ ከሳምኳቸው በኋላ እንድታቆም በአንደኛው እጄ
ያዝኳት። ወደጆሮዬ ተጠግታ
"ምንም አልሆንም‘ኮ ……… እሺ በለኝ ስሞትልህ……ናፍቀኸኛል…
" ሹክሹክታዋ ይነዝራል። እጇን ለቀቅኩላት። እኔ ማንበቤን
ቀጠልኩ እንደማትሰማኝ አውቃለሁ። ……… በአንደኛው እጇ
ስትነካካኝ ማንበቤን የት ቦታ እንዳቆምኩት አላስታውስም።……
ሲኦል እየታየኝ መሳቄን ወደድኩት……… ኤልሲ እንደራበችኝ እንጂ
ሌላ ማሰብ እንደነበረብኝ አልተገለጠልኝም። ………… ራቁቷን
አልጋው ላይ ተንጋላ ከነፍሷ እየፈገገች ታየኛለች።………
እስከየትኛው ቅፅበት ትንፋሿን እንደሰማሁት አላስታውስም። ……
"ፍቅሬ እንዴት ላድርግሽ? እርበሽኛል ………" አልመለሰችልኝም።
ትንፋሿ ደክሟል። ራሷን ስታለች።……
ኤልሲ በሆነው ባልሆነው የሚከፋት ነጭናጫ እየሆነች መጣች።
የእኔ ለውጥ:—
ኤልሲን ይበልጥ በፍቅር አበድኩላት። አንጀቴ ስፍስፍ ይልላት
ጀመር። ለምንም ሰዓት ትቻት ባልሄድ ደስ ይለኛል።
ያልገባኝ ነገር አልነበረም። ሁሉም ለውጥ ግልፅ ሆኖ ይገባኛል።
ግን የፍቅሬ መጨመር የማይካድ ለውጥ ነው።
ኤልሲን ከነዚህ ሁሉ ለውጦች በፊት አውቃታለሁ። ዛሬ እንደጨው
እጄ ላይ ይቀልጣል ብዬ የምሳቀቅበት ገላዋ ትናንት የእርካታዬ
ጥግ ነበር። ብቻዬን የማውቀው የኔ ብቻ……… አመት እንደቀልድ
ነጎደ።
በዚህ ወቅት ነው ልታገባ እንደሆነ የነገረችኝ። ብዙም ሳትቆይ
ከሀገር ወጣች። …… …… ነፍሴም ከስጋዬ ተፋታ… … አብሯት
ከሃገር ወጣ……… በቀረው ስጋዬ… … …… አገባሁ፣ ሁለት ልጆች
ወለድኩ………… ዛሬ ሆነ።
ይሐው ከኤልሲ ጋር ………… ሆስፒታሉ ውስጥ…………………
"ስለማፈቅርህ!! እመነኝ ከራሴ ይልቅ ላንተ ስላደላሁ ነው።
ባልተውህ አትተወኝም። የራስህን መኖር ገድለህ ከኔ ጋር
ስታ

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ትኬቱን ለማግኘት በ0922870815 ላይ ይደውሉ

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ፍካሬ-ሃኬት

በክብረት ሙሉጌታ
.
.
የስንፍና መንፈስ የቅሽመት ውቃቤ
ግዝፈ ስጋ ነስቶ   ቆሞ   ካጠገቤ
በሰመመን መሃል
እንደዚህ ይለኛል............
      **   **    **
እውቀትን የለካ
ሰነፍን   የነካ
የሰነፍ መዶሻ
ከበተስኪያን ቅጥር እንደ ገባ ውሻ
ጥበብ ያነገበ የምሁር ጭንቅላት
 ይሰደድ አውግዙት
 እንደ ማርያም ጠላት
 ጥበብ ጥበብ ያለ
የብራና መጣፍ በጀርባው ያዘለ
ዚቅን የዘለቀ
ሊቁን ያደነቀ
ያሬድን ያወቀ
ከጥንታዊው ደብር ከተራራው ይውረድ
 ከቀየው ይሰደድ                
 ሌላው ይቅርና
 ሌላው ይቅርና
ጥበብን የያዘ የምስጢር ብራና
እርሱንም ስደዱት
አቦ እንስነፍበት!
................ይለኛል

   **  **  **

የስንፍና መንፈስ የቅሽመት ውቃቤ
ግዝፈ ስጋ ነስቶ   ቆሞ   ካጠገቤ
በሰመመን መሃል
እንደዚህ ይለኛል...........

     **   **   **
 መጦመር ያበዛ
የ “ተንስዑ” መልዕክት በህዝቡ የነዛ
ያላረፉ ጣቶች ብራናን የፋቁ
 ከክታብ ያልራቁ
  ጭብጨባን ያስናቁ
   ብዕር የጨበጡ
    ቀለም የቀየጡ
ያላረፉ ጣቶች አርፈው ይቀመጡ 
ይኸዉ!        ቀለም በጠበጡ
                  ቀለም በጠበጡ
              ቀለም የቀየጡ
የቀለም አብዮት አመጽን ያመጡ
ያላረፉ ጣቶች  አሁን ይቆረጡ !
................ይለኛል
ጸሐፊው  ተሰድዶ ምንጩ ከደረቀ
ብራናው ተሽጦ ዥረቱ ካለቀ
ይህን ብቻ ሰርተን
 አብረን እንሰንፋለን  
  እያለ ይለኛል
እያለ ይለኛል ወኔ ያሳጣኛል

     **   **   **

የስንፍና መንፈስ የቅሽመት ውቃቤ
ግዝፈ ስጋ ነስቶ   ቆሞ   ካጠገቤ
በሰመመን መሃል
እንደዚህ ይለኛል...........
    **   **   **
ጥንተ ታሪክ አጥፉ ይሰበር ድልድዩ
ያባቶችን ጥበብ    ልጆች እንዳያዩ
ከዚያስ?   
ከዚያማ!.....
በፈጠርነው አለም በራሳችን ሜዳ
 በስንፍና ጓዳ
ጥበብን የሚረግጥ
ሂስ ተግቶ ’ሚውጥ
ጥያቂ ሚፈራ
ትውልድን እናፍራ
ያ......ትውልድ!
ቀጥቅጠን ብንገዛው
ሺህ ጊዜ ሺህ አመት
 በፈለግነው ስርዓት
  ባሰብነው ርዮት
ሞኝ.........ትውልድ!
እንኳን ሞፈር መቁረጥ እንኳን ከደጁ ዛፍ
እንቡጥ ፍቅሩን ብትቀጥፍ
ከደሙ ብትጨልፍ
 ከደሙ ብትቀዳ
ጥያቄን  ይፈራል እንዴትም  ቢነዳ
“እንዴ ት”ን አያውቅም ያ!ቀሽም አራዳ 

https://t.me/joinchat/AAAAAEGznayjbWng0o2h7Q

Читать полностью…

ዐውደ ጥበብ

ጣፋጭ እና የተወደዱ ኢስላማዊ ታሪኮች ምርጫዎን ጠቅ በማድረግ ይጎብኟቸው

👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…
Подписаться на канал